ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው መስመር ጥገና ተጠናቀቆ አገልግሎት ጀመረ

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) ከካራቆሬ እስከ ከሚሴ ያለው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮቹንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ከሥርጭት ኔትወርክ መስመሮች ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ በርብርብ ሲሰራ ቆይቶ ዛሬ እስከ ከሚሴ ድረስ ያሉት ከተሞች ኃይል ማግኘት ችለዋል፡፡

የጥገና ሥራው ወደ ደሴ ከተማ ቀጥሎ እስከ ሀርቡ ባለው አካባቢ መስመሮችን የመጠገን ሥራም እየተካሄደ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በሚሌ ባቲ ያለው መስመር ላይ ሁለት ኃይል ተሸካሚ ምሶሶዎች በከባድ መሳሪያ በመመታቸውና ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ምሶሶዎቹን እንደገና የመትከል ስራ ተጀምሯል።