ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ጥቅም አይገኝም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

መጋቢት 14/2013 (ዋልታ) – በማንኛውም መመዘኛ ከጦርነት ጥፋትና ኪሳራ እንጂ ጥቅም አይገኝም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ኦሮሞና አማራን ለማጋጨት የተደራጁ  አካላት እንደሚንቀሳቀሱ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን በመረዳት በሁለቱ ክልሎች መካከል ችግር ሲፈጠር ክልሎቹ ተባብረው በመስራት የጠላትን አላማ ማክሸፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕግ ማስከበር ዘመቻው 300 የሚጠጉ የኦነግ ሸኔ ሽፍታ ቡድን አባላት ትግራይ ውስጥ ሲዋጉ እንደነበር ጠቁመው፣ ኦነግ ሸኔ የኢትዮጰያ ጠላት ነው ነው ብለዋል፡፡

ኦነግ ሸኔ ከአማራ ህዝብ በላይ የኦሮሞን ህዝብ ጎድቷል ፤ ቡድኑ የወለጋ ህዝብ መንገድ እንዳይሰራለትም አድርጓል፡፡

በአጠቃላይ ይህ ቡድን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

የወለጋ ህዝብ በኦነግ ሸኔ ስቃይ ውስጥ ነበር ፤ ወለጋ ውስጥ የሞቱት አማራዎች  ሳይሆኑ የኦሮሞ አካል ናቸው፤ እነሱን መግደል ኦሮሞን መግደል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

(በብርሃኑ አበራ)