ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች በአማራ ክልል በቡልጋ እና በደብረብርሃን ከተሞች የሚገኙ ነባር የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው፡፡
በጉብኝቱ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል አመራሮች መገኘታቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!