ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ ዛሬ እንደሚጀመር ተገለጸ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) በተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ ዛሬ በይፋ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወቅታዊ ጉዳዮችን በማስመልከት ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት መግለጫ በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በቅርቡ 12ሺሕ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
ዜጎቹን ለመመለስም የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ዐቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ወደ ሀገራቸው የሚመለሱት ዜጎችም ከታንዛኒያ ፣ ጅቡቲ ፣ ማላዊ ፣ ኦማን እና ከሌሎች አገራት መሆኑንም ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡