ከ18 ሺህ ኩንታል በላይ ስንቅ ለሠራዊቱ ድጋፍ ተደረገ

ነሃሴ 13/2013 (ዋልታ) – የደቡብ ወሎ ዞን ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ለሠራዊት አባላት ከ18 ሺህ ኩንታል በላይ ደረቅ ሬሽን  ድጋፍ አድርጓል፡፡

እስካሁን የተዘጋጀውን ከ18 ሺህ ኩንታል በላይ ስንቅ ተሰብስቦ ለሠራዊቱ እንዲደርስ መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ አስታጠቅ ግዛው  ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የሚገኙ ሴቶች ስንቅ ከማዘጋጀት ባለፈ ስልጠና በመውሰድ ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑንም ኀላፊዋ መግለጻቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

አሁንም በህልውና ዘመቻው ላይ ግንባር ለሚገኘው ሠራዊት መደገፋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡