ከ200 ኩንታል በላይ አደንዛዥ እፅ መወገድ በሁመራ

አደንዛዥ እፅ መወገድ በሁመራ

መስከረም 10/2014 (ዋልታ) ከ200 ኩንታል በላይ አደንዛዥ እፅ ማስወገዱን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስታወቀ፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ሕጻናትን አደንዛዥ እፅ እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል።

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በተለያየ ጊዜ ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን ተደራሽ ሊሆን የነበረን ከ200 ኩንታል በላይ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር በማዋል በዞኑ በተዋቀረው ኮማንድ ፖስት አማካኝነት መወገዱን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የሕዝብ ሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኅላፊ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ገልጸዋል።

በዞኑ የአሸባሪው ቡድን እንቅስቃሴና ትንኮሳ የጸጥታ ኀይሉ በንቃት እንደሚቆጣጠር ገልጸው፣ ወልቃይት ለአሸባሪው ቡድን መቀበሪያው ይሆናልም ብለዋል።

የ63ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አሸባሪው እና ወራሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ መግለፃቸውን አሚኮ ዘግቧል።