ከ39.6 ቢሊየን ብር በላይ የሚተመኑ የግብርና ምርቶች ተገበያይተዋል – ምርት ገበያ

ሐምሌ 08/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2013 ዓ.ም ከ39 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያወጡ 614 ሺህ 586 ሜትሪክ ቶን የግብርና ምርቶችን በማገበያየት የበጀት ዓመቱን አጠናቀቀ፡፡

ምርት ገበያው በምርት መጠን 96 በመቶ፣ በዋጋ 102 በመቶ በማከናወን ዕቅዱን ማሳካቱ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወንድማገኝ ነገራ ከተገበያየው የምርት መጠን ውስጥም ቡና 35 ነጥብ 5 በመቶ ሰሊጥ 31 በመቶ ሌሎች ጥራጥሬዎች 33 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ አላቸው ብለዋል።

ምርት ገበያ በአዲሱ ዓመት የማዕድን ግብይትንም ለመጀመር ከማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ሰንድ እንደተፈራረመ አቶ ወንድማገኝ ነገራ ገልጸዋል።

አክለውም በ2014 ዓ.ም አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል፡፡

(በደምሰው በነበሩ)