ከ400 ሺሕ ዶላር በላይ ወጪ የተገነባው አብዲ ቦሩ የመዋለ ህፃናት ተመረቀ

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) በአረብ ኤምሬቶች ድጋፍ በሮቤ ከተማ ከተገነቡ መሠረተ ልማቶች መካከል አንዱ የሆነው አብዲ ቦሩ የመዋለ ህፃናት ተመረቀ።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የአረብ ኤምሬት ዓለም ዐቀፍ ቀይ ጨረቃ ዋና ፀኃፊ ፉአድ አብዱረህማን በከተማው የተገነቡ ፕሮጀክቶችን እየመረቁ ነው፡፡

በከተማዋ ከተገነቡ መሠረተ ልማቶች አንዱ የሆነው አብዲ ቦሩ የመዋለ ህፃናት የመረቁ ሲሆን ከ330 በላይ ህፃናት ያስተናግዳል ተብሏል፡፡

ትምህርት ቤቱ ዘመናዊ የመዋለ ህፃናት ሲሆን ከ412 ሺሕ ዶላር በላይ ወጭ ተደርጎበታል።

ሚልኪያስ አዱኛ (ከሮቤ)