ከ400 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ድጋፍ ተደረገ

ሚያዝያ 5/2014 (ዋልታ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ለሚገኙ ከ400 በላይ አቅመ ደካማ ዜጎች በወረዳው ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር በመሆን ከ600 ሺሕ ብር በላይ ግምት ያላቸውን የዘይት፣ ዱቄት፣ ማካሮኒ እና ፓስታ የምግብ አይነቶችን ድጋፍ አደርጓል፡፡

ድጋፉ የተደረገው በሀገሪቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣውን የኑሮ ዉድነት ከግምት  ውስጥ በማስገባት የመረዳዳት ባህልን ለማዳበር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በሀገሪቱ እያጋጠመ ላለው የኑሮ ውድነት ችግር አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የከፈተው ጦርነትና የዓለም ዐቀፍ ተፅዕኖ ዋና ምክንያት መሆኑን የወረዳ 12 ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰብለወርቅ  ታደሰ ተናግረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ የኑሮ ውድነት ችግሩን ለመቅረፍ እርስ በርስ መደጋገፍ እንደሚገባና በተለይም የጓሮ አትክልቶችን በመትከልና በማልማት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ድጋፉን ላበረከቱ ባለሀብቶች ክፍለ ከተማው የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል፡፡

በአመለወርቅ መኳንንት

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!