ጥር 19/2014 (ዋልታ) ከ404 ሺሕ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ መልማቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ዑመር ሁሴን በመጀመሪያ ዙር በመስኖ ለማልማት ከታቀደው 400 ሺሕ ሄክታር መሬት ውስጥ ከእቅድ በላይ መሳካቱን አስታውቀዋል።
የዕቅዱን 101 በመቶ በማሳካት በመጀመሪያው ዙር የመስኖ ልማት 404 ሺሕ 900 ሄክታር መሬት በመስኖ እንደለማ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ይህ እንዲሳካ ላደረጉ አርሶ አደሮች ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ የበጋ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እንደሚከናወንና በሌሎች የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል።