ካውንስሉ በምስረታው ዕገዛ ላደረጉ ተቋማት ዕውቅና ሰጠ

የካቲት 13/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ካውንስል በምስረታው ዕገዛ ላደረጉ የግልና የመንግስት ተቋማት ዕውቅና ሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ካውንስል ከተመሰረተ አንድ ዓመት አስቆጥሯል፡፡

እስካሁን 35ሺህ ቤተ እምነቶች በተናጠል ሲሰሩ ነበር ቢሆንም ካውንስሉ እነዚህን ቤተ እምነቶች በማካተት ሃይማኖታዊና የልማት ስራዎችን ለመስራት የተቋቋመ ነው ተብሏል፡፡

ካውንስሉ በሃገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ አባላቱን በማስተባበር ጤናማና ተተኪ ትውልድ ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከሌሎች አቻ የሃይማኖት ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይ መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ በተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይ ለመስራት መዘጋጀቱን ካውንስሉ አስታውቋል፡፡

(በተስፋዬ አባተ)