ክልሉ በኅልውና ዘመቻ ለተሳተፉ የልዩ ኃይል አባላት ዕውቅና እና ሽልማት አበረከተ

የልዩ ኃይል አባላት ዕውቅና

ሐምሌ 25/2014 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በኅልውና ዘመቻው ለተሳተፉ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትና አመራሮች የዕውቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡

በመርኃ ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወንድሙ ኩርታና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የሕወሓት አሸባሪ ቡድን የከፈተውን ወረራ ተከትሎ መንግሥት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ግዳጅ ቀጣና ተሰምርተው የነበሩ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትና አመራሮች የተሰጣቸውን ግዳጅ በቁርጠኝነት ፈፅመው ሀገርን ከማፍረስ መታደግ መቻላቸው ተነስቷል፡፡

የዕውቅና እና ሽልማት መርኃ ግብሩም በግዳጅ ቀጣና ተሰማርተው ተልዕኳቸውን አጠናቀው ለተመለሱ የልዩ ኃይል አባላትና አመራሮች የተዘጋጀ መሆኑን ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW