ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ታሪክ 760 ግቦችን በማስቆጠር የዓለማችን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረሰወሰንን ለመያዝ ችሏል።
የዘንድሮውን የጣልያን ሴሪአ በ15 ግቦች ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን እየመራ ያለው የ35 ዓመቱ ሮናልዶ በቅርቡ ነበር ብራዚላዊውን ፔል ያስቆጠራቸው 757 ግቦችን መብለጥ የቻለው።
ክለቡ ጁቬንቱስ ትላንት ናፖሊን 2ለ0 በመርታት የጣልያን ሱፐርካፕ ዋንጫን ለ9ኛ ጊዜ ሲያነሳ ሮናልዶ አንዷን ግብ ማስቆጠር ችሏል ሲል ስካይ ስፖርት ዘግቧል።
ቼክ ሪፑብካዊው ጆሴፍ ቢካን በ759 ግቦች 2ኛ፣ ብራዚላዊው ፔሌ በ757 ግቦች 3ኛ፣ ብራዚላዊው ሮማሪዮ በ743 ግቦች 4ኛ፣ አርጅንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ በ719 ግቦችን በማስቆጠር 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።