ክፍለ ጦሩ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) በደቡብ ዕዝ የሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ።

የሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ በየትኛውም ጊዜና ሰዓት መንግሥት በሚሰጠን ትዕዛዝ መሰረት አሸባሪም ይሁን ወራሪ ኃይልን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ዋና አዛዡ አክለውም ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ለእግረኛ ኃይላችን የተኩስ ድጋፍ ለመስጠት እና በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁነቱን አረጋግጧል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW