ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የ2021 የጀርመን አፍሪካ ሽልማትን ተቀበሉ

ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)

ኅዳር 11/2014 (ዋልታ) የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በርሊን ብራንድቡርግ የ2021 የጀርመን አፍሪካ ሽልማት ተቀብለዋል።

ኮሚሽነር ዳንኤል ሽልማቱን ያገኙት በህይወት ዘመናቸው ለሰብአዊ መብት መከበር ባደረጉት ከፍተኛ ትግል ነው ተብሏል።

የሽልማቱ አሸናፊ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) «ሽልማቱ  ለሰብአዊ መብቶች መከበር በየቀኑ ለሚሰሩ እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲሁም በፖለቲካዊ ተቃውሞ ውስጥ እንኳን ሆነው የእኩልነት መርህን ለሚጠብቁ ባልደረቦቻቸው ሁሉ ይሁን» ሲሉ ተናግረዋል።

የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን ዳኞች ፕሬዝዳንት ክላውስ ሽቴከር በበኩላቸው «ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኃላፊነት እና ድፍረት ምሳሌ ሲሉ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)ን አሞግሰዋቸዋል።

ኮሚሽነሩ ምን ያህል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ስራቸውን እያከናወኑ እንደሆነም ሽቴከር አውስተዋል።

ሽልማቱን የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ኡሺ አይድ እና የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን ዳኞች ፕሬዝዳንት ክላውስ ሽቴከር በጋራ ለዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ማበርከታቸውን ዶቼቬሌ ዘግቧል።