ኮሚሽኑ በችግኝ እንክብካቤና የተቋማት ተሳትፎ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው

ሚያዝያ 06/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ኮሚሽን በችግኝ እንክብካቤና የተቋማት ተሳትፎ ላይ ከተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ሲሳይ ጌታቸው በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባን ምቹ እና አረንጓዴ የማድረግ ስራዎች እየተሰራ መሆናቸውን ገልጸው፣ በዚህም በመዲናዋ 8.5 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።

እነዚህን ችግኞች ለመትከል 426 ተቋማት ተሳታፊ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ሲሳይ፣ ከተተከሉት 8.5 ሚሊየን ችግኞች መካከል 83 በመቶ  መፅደቁን አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ በአረንጓዴ ልማት ላይ የተሰሩ የዳሰሳ ጥናት ይቀርባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በአረጓዴ ልማት ላይ አስተዋፆ ያበረከቱ ተቋማት እውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።

በቀጣይም በአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት የሚሰሩ ስራዎች ላይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተመላክቷል።

(በሱራፌል መንግስቴ)