ኮሚሽኑ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ከንግድ ማጭበርበር ማዳን መቻሉን ገለጸ

ነሃሴ 4/2013 (ዋልታ) – በተጠናቀቀው በጀት አመት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ከኮንትሮባንድና ንግድ ማጭበርበር ማዳን መቻሉን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባድ እንቅስቃሴንና  ህገ ወጥን ንግድ ማጭበርበርን በቅንጅታዊ አሰራር ለመከላከል በ2013 በጀት አመት የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌደራል ፖሊስ አመራሮች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡

በውይይቱም ኮሚሽኑ በበጀት አመቱ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለማዳን አቅዶ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ ከእቅድ በላይ ማሳካቱን ተገልጿል፡፡

ኮሚሽኑ በቀጣዩ በጀት አመት አጠቃላይ 155 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ያስቀመጠውን እቅድ ለማሳካት በተሰራው ስራ የታዩ ጠንካራ ስራዎችን ማስቀጠልና መታረም ያለባቸውን ክፍተቶች ማስተካከል ከተቻለ የበለጠ ውጤት ለማምጣት እንደሚያስችል ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡