ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከ35 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል አመቻቸ

ሐምሌ 01/2013 (ዋልታ) – የሰው ሀይል በማቅረብና ሀብት በማስተዳደር ላይ የተሰማራው ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ከ35ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል በማመቻቸት ሀገራዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገለፀ።

ድርጅቱእየሰራቸው ባላቸው ስራዎችና እንቅፋቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ30 በላይ ቅርጫፍ ቢሮ ያለው ኮሜሪሻል ኖሚኒስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ13 ባላነሰ የስራ አይነቶች ላይ የሰው ሀይልን በማቅረብና ሀብትን በማስተዳደር ላይ ተሰማርቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመከረበት መድረክ ላይም ሰራተኛና አሰሪን በማገናኘትና ሌሎች አገልግሎትንም በመስጠት የበኩሉን ሀገራዊ ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑ ተነስቷል።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ በስራ ላሰማራቸው ከ35ሺህ በላይ ሰራተኞች መንግስት ያስቀመጠውን የ20/80 አሰራር ከሞላ ጎደል ተግባራዊ እያደረገ ነው የተባለ ሲሆን ሌሎች ቀሪ ጉዳዮችን በሂደት ለማሟላት እንደሚሰራም ተገልጿል።

(በደምሰው በነበሩ)