ኮርፖሬሽኑ ከ1 ሺሕ በላይ መፃህፍት ለአብርሆት ቤተ መጽሐፍ አበረከተ

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) ትኩረታቸውን በኢንጂነሪንግና በሳይንስ ዘርፍ ያደረጉ ከአንድ ሺህ በላይ መፃህፍትን ለአብርሆት ቤተ መጽሐፍ ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አዲሱ ማሞ እንደገለጹት፤ ኮርፖሬሽኑ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለአንድ ወር ያህል ሲያካሂድ በቆየው የማሰባሰብ ስራ ያገኛቸውን እና ለትውልድ ይጠቅማሉ ያላቸውን መጽሐፍት አስረክቧል።

ለቤተ መጽሐፉ የተበረከቱት መጽሐፎች በኢንጂነሪንግና በሳይንስ ዘርፍ ትኩረት የሚያደርጉ ናቸው።

መጽሔቶችን ለማሰባሰብ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሀብቶችን ማህበራዊ ኃፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የማስተባበር ሥራ ተሰርቷል ማለታቸውን የኢፕድ ዘገባ አመላክቷል፡፡