ኮርፖሬሽኑ የ9 ወራት አፈጸጸሙን ባቀደው መሰረት ማከናወኑን ገለጸ

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጸጸሙ ባቀደው መሰረት ማከናወኑን ገለጸ፡፡
ኮርፖሬሽኑ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡
ግምገማው ተቋሙ በአራት አመታት ውስጥ በካሄደው ውጤታማ ተቋማዊ ማሻሻያ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል እና ተጨማሪ የመፈጸም አቅም መገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በተሰማራባቸው በአራቱም የሥራ ዘርፎች ማለትም በቤት ልማት ፣በቤት አስተዳደር ፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት እና ሰርቪስ ዘርፎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ በእቅዱ መሰረት ሥራዎች መሰራታቸው ተገምግሟል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በአገር ዓቀፍ ደረጃ ጎልቶ የወጣበት የቤት ልማት ዘርፉ በፕሮጀክት አስተዳደር ፣ በግንባታ ቴክኖሎጂ ረገድ የታየው የላቀ አፈጸጸም በጥንካሬ ተነስቷል፡፡
በአስራ ስምንት ወራት ግዙፍ የመኖሪያ መንድር መገንባት መቻሉ ለአብነት የተነሳ ሲሆን በዚህም የግንበታ ፍጥነት ፣ጥራት እና ቅልጥፍና እንዲሁም የግንባታ ቴክኖሎጂ መጠቀምን በቀጣይም የኮርፖሬሽኑ የቤት ልማት ዘርፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡
በቤት አስተዳደር ረገድም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሥራ ቦታን ምቹ የማድረግ፣ ከፍተኛ የሆነ የገቢ እድገት ጭማሪ ማሳየታቸው እና እተገነባ ያለው የመፈጸም አቅም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በግምገማው ተጠቁሟል፡፡
የኮስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ለቤት ልማት ዘርፉ የተሰላጠ የግንባታ ግብዓት ከማቅረብ በሻገር ተጨማሪ ገቢ ኮርፖሬሽኑ እንዲያገኝ ገቢ ማግኛ ዘዴዎችን እያሰፋ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ንብረት በሕግ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች እና በሕገ-ወጦች እንዳይወሰድ በሕግ አግባብ ክትትል በማድረግ የሕዝብና የመንግሥት ጥቅም የማስከበር ተግባር የሚያስቀጥሉ ተጨማሪ ሥራዎች እንዲሰሩ ነው የተባለው፡፡
ግምገማው በቀጣይ ወራቶች እንዲተገበሩ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችና የአሰራር ስልቶች መቀመጡን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል::