መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ ህብረተሰቡ መከላከያ ዘዴዎችን ሙሉ ለሙሉ እንዲተገብር የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የኮቪድ-19 መከላከያ ዘዴዎችን ሙሉ ለሙሉ ማስተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከፌደራልና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ነው የተወያዩት፡፡
ውይይቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በተመለከተ ከተጋረጠው ስጋት ለመውጣትና ህዝቡን ለመታደግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡