ኮትዲቫር በማሊ የሚገኘውን ሰላም አስከባሪ ጦሯን በዚህ ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ እንደምታስወጣ አስታወቀች

ኅዳር 7/2015 (ዋልታ) ኮትዲቫር በአሚሶም ጥላ ስር የሚገኙትን ወታደሮቿን ቀስ በቀስ ከማሊ እንድምታስወጣ ስታስታውቅ እስከ ነሐሴ ወር ድረስ ግን ወታደሮቿ ሙሉ ለሙሉ ከማሊ እንደሚወጡ አስታውቃለች፡፡

ሀገሪቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በአቢጃን እና ባማኮ መካከል የተፈጠረውን የዲፕሎማሲ መሻከርን ተከትሎ ነው፡፡

ባለፈው ሐምሌ ወር በዋና ከተማ ባማኮ ማሊ 49 የኮትዲቫር ወታደሮች ማሰሯን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት በውዝግብ ውስጥ የገቡ ሲሆን ማሊ ከታሰሩት ወታደሮች መካከል ሦስቱን ስትለቅ ቀሪዎቹን አሁንም እንዳሰረች ነው የተገለጸው፡፡

በተመሳሳይ እንግሊዝም በማሊ ያላትን ወታደሮች እንደምታስወጣ ያስታወቀች ሲሆን ሀገሪቱ 300 ወታደሮች በማሊ እንዳላት ተመላክቷል፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2012 ጀምሮ ማሊ በፅንፈኞች ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርስባት ሀገር ስትሆን ሀገሪቱን ለማረጋጋት የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲገባ መደረጉን የአፍሪካ ኒውስ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW