የካቲት 16/2013 (ዋልታ) – ፈጣሪ ገነት አድርጎ የፈጠራትን ኮንታ አለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጂማ-ጪዳ የ80 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ስራን የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሃ ግብሩ ላይ ምድራዊ ገነት የሆነችውን ኮንታ አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የጂማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱልሃኪም ሙሉ የጂማና ኮንታ ህዝቦች ወንድማማች እንደሆኑ ጠቅሰው የመንገዱ መገንባት በአካባቢው ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡
የኮንታ ልዩ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፋንታሁን ብላቴ በበኩላቸው መንገዱ በጎርፍና የመሬት መንሸራት በተደጋጋሚ እየተዘጋ ያስቸግር እንደነበር አስታውሰው፣ በዚህ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት ግንባታው መጀመሩ ለነዋሪዎቹ እፎይታ ነው ብለዋል፡፡
(በዮሴፍ ታደሰ)