ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

ግንቦት 22/2014 (ዋልታ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 915 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።

ተማሪዎቹ የመጡበትን ዓላማ አሳክተው ለመመለስ መዘጋጀታቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ከፍተኛ ውድመት ደርሶበት የነበረና በመልሶ ግንባታ ወደ ስራ የገባ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል።