ወታደራዊ ሥልጠና ዝግጁነትን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

ወታደራዊ ሥልጠና

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የተደረገው ወታደራዊ ሥልጠና ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና አለው ሲሉ በደቡብ ዕዝ የኮር ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ነገሪ ቶሊና ገለጹ።

ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ አመራሮች በመታገዝ የተደረገው ወታደራዊ ሥልጠና የሠራዊቱን የማድረግ አቅም ከማሳደጉ በተጨማሪ የተጣለበትን ሀገራዊ አደራ በብቃት ለመወጣት ያስችለዋል ብለዋል።

በከፍተኛ ጥናት ላይ ተመሥርቶ ለወራት ሲደረግ በቆየው የተቀናጀ ወታደራዊ ልምምድ ሠራዊቱ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው የገለጹት ሜጀር ጄኔራል ነገሪ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁነቱ የላቀ ነው ብለዋል።

ሥልጠናውን ከተሳተፉ አመራሮች መካከል ሌተናል ኮሎኔል መለስ ሙሉ እና ሻለቃ ተክለጻዲቅ በበኩላቸው ሥልጠናው በተግባር ተደግፎ በተለያየ መልከኣ-ምድር እና የአየር ፀባይ መሰጠቱ ሠራዊታችንን ለማንኛውም ተልዕኮ ዝግጁ ያደርገዋል።

በተከታታይ ወራት ባደረግናቸው ሥልጠናዎች ከፍተኛ አቅም ገንብተናል ያሉት አመራሮቹ በአሁኑ ወቅት ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ለመፈፀም በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW