ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንና ዳያስፖራዎች ያሳደሷቸውን ቤቶች አስረከቡ

ጥር 21/2014 (ዋልታ) ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ከዳያስፖራዎች ጋር በመተባበር ያሳደሳቸውን የአረጋዊያን ቤቶች ለነዋሪዎች አስረከበ፡፡
ፋውንዴሽኑ ዛሬ ያስረከባቸው ቤቶች 15 ሲሆኑ ለ40 ዓመታት ያህል ሳይታደሱ የቆዩና ለኑሮ ምቹ ያልነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በርክክብ ስነ ሥርዓቱ ላይም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ እና የእስልምና ሃይማኖት መምህር ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ጨምሮ ዳያስፖራዎች ተገኝተዋል፡፡
ኢዜአ እንደዘገበው በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ዳያስፖራዎች ወንድም ካሊድ ፋውንዴሽንን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡