ወደ ትግራይ የምግብ ዕርዳታ ይዘው የገቡ የጭነት መኪናዎች 277 መድረሳቸው ተገለጸ

ነሃሴ 05/2013 (ዋልታ) – ወደ ትግራይ ክልል የምግብ ዕርዳታን ይዘው የገቡ የጭነት መኪናዎች 277  መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡

መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም አደርጎ ከትግራይ ከዋጣ በኋላ ህወሀት የእርዳታ እህል ለትግራይ ህዝብ እንዳይደርስ ሲያስተጓጉል መቆየቱ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ህወሐት ፀብ አጫሪነቱን ካቆሙ እርዳታ ወደ ክልሉ እዲደርስ ማንኛውንም አማራጭ እጠቀማለሁ ሲል መግለጹም አይዘነጋም፡፡