ወጣቶች በ6ተኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ነገን የተሻለ ሀገር ለመገንባት የድርሻቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

ግንቦት 13/2013(ዋልታ) – የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ቀጣዩን 6ተኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በማስመልከት የወጣት እጩዎች የትዉዉቅና የይምረጡኝ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ በጌዴኦ ዞን በዲላ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በእጩዎች የትዉዉቅና በይምረጡኝ ቅስቀሳ በድጋፍ ሰልፍ ላይ ከዞኑ ማዕከል ከሁሉም ወረዳዎች የተወጣጡ በርካታ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

የወጣት እጩዎች የትዉዉቅና የይምረጡኝ ቅስቀሳ በድጋፍ ሰልፍ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ደግነት ሃይሉ እንደተናገሩት  ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ነፃነቷን ጠብቃ የኖረች ሀገር በመሆና ወጣቶች በ6ተኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ነገን የተሻለ ሀገር ለመገንባት የድርሻቸዉን መወጣት አለባቸዉ ብለዋል፡፡

በተለይ አሁን በሀገር ደረጃ የተጀመረዉን የለዉጥ ጉዞ በዘላቅነት ለማስቀጠል የወጣቱ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ሃላፊዉ  ክብሯንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ የኖረችዉን ሀገር ለቀጣይ ትዉልድ  ለማሻገር ወጣቱ በ6ተኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ የበኩሉን መወጣት እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡

(በደረሰ አማረ)