ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ነሃሴ 06/2013 (ዋልታ) –  የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዶክተር አላስታየር ማክፊልን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የሰብዓዊ ድጋፍ በተፋጠነ መልኩ ማስተባበር፣ ተደራሽነትን ማሳደግን እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።