ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስታር ማክፋይል ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው መንግሥት በከተሞች የሚታየውን የሥራ አጥነት፣ የመኖሪያ ቤት ዕጥረትና ከሰላም ጋር በተያያዘ እያደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ መክረዋል፡፡

አምባሳደር አላስታር ማክፋይል መንግሥት በቀጣይ 10 ዓመት በከተሞች የያዛቸውን ዕቅዶች ለመተግበር በሚያደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።