ውጤታማ ለሆኑ መስመራዊ መኮንኖች የማዕረግ እድገት

መኮንኖች የማዕረግ እድገት

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) በአየር ኃይል የምዕራብ አየር ምድብ በስራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ መስመራዊ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ተሰጠ።

የምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ቸርነት መንገሻ፤ለተሿሚዎቹ ማዕረግ ካለበሱ በኋላ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ሽብርተኛ ለመደምሰስ በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ምድቡ ለትውልድ የሚተላለፍ ጀብድ ፈፅሟል ።

የምድቡ ሰራዊት “ሰው እስኪደክመው ይሰራል ወታደር ግን ለአገሩ ለቆመለት አላማ ህይወቱ እስኪሰዋ ይሰራል “የሚለውን ብሒል የአላማ ፅናትን፣ ቅንነትን፣ ታማኝነትንና ቆራጥነትንና ፍፁም ሕዝባዊነትን የበለጠ በመላበስ ምድቡ የሚሰጣችሁን ግዳጅ መወጣት ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡

የምዕራብ አየር ምድብ የሠው ሐብት ልማት ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አበበ ኃይሉ ”በቀጣይ ብቃታችሁንና ክህሎታችሁን ተጠቅማችሁ ዜጎችን ሰላምና ጤና በመንሳት የኢትዮጵያን ደስታና ተስፋ ለመንጠቅ የሚጥረውን አሸባሪ የህዋሃት ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ዘመቻ ዝግጁነታችሁን ማጠናከር ይገባችኋል” ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።