ዓለም አቀፍ የመረጃ ነፃነት ቀን በመረጃ አሰጣጥ ሂደት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከበር ተገለጸ

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) ኅዳር 18 ቀን ዓለም አቀፍ የመረጃ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ ለ4ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ6ኛጊዜ እንደሚከበር የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

የመረጃ ነፃነት ቀን ሲከበር ዋና ዓላማው የመረጃ ነፃነት ማግኘት ህገ-መንግስታዊ መብት መሆኑን ትኩረት ለመስጠት፣ የመንግስት ተቋማት እና ድርጅቶች ለዜጎች አስፈላጊውን መረጃ መስጠት እንዳለባቸው እንዲሁም ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የመረጃ አሰጣጥ ሂደት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ዘውዱ ወንድም ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ ተቋማት መረጃን ለሚመለከታቸው አካላት በሚከለክሉበት ጊዜ የእንባ ጠባቂ ተቋም አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት ዳይሬክተሩ የመረጃ ነፃነት መርሆዎች እንዲከበሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት