ዓለም ዐቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ 2ኛ ዙር የህክምና ቁሳቁስ ወደ መቐለ መላኩን አስታወቀ

ጥር 20/2014 (ዋልታ) ሁለተኛ ዙር አስቸኳይ የህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ መላኩን የዓለም ዐቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
ኮሚቴው በትላንትናው ዕለት ሁለተኛው ዙር አስቸኳይ የህክምና ቁሳቁስ በአውሮፕላን መቐለ ማድረሱን በማኅበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
ተቋሙ በመጀመሪያ ዙር ድጋፉ መድኃኒቶችን ጨምሮ የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ቁሳቁስ ጥር 18/2014 ዓ.ም መቐለ ማድረሱን ከተቋሙ ድረገጽ ለማወቅ ተችሏል፡፡