ዘመቻ በትምህርት ልማት ግምባር በድል ተጠናቋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ታኅሣሥ 4/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ከ30 ሺሕ በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርቱ ማኅበረሰብ አካላት የተሳተፉበት ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር ከፍተኛ የአገር ፍቅር ወኔና ተነሳሽነት በታየበት አፈፃፀም በድል መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በዘመቻው ተካፋይ የነበሩ ተማሪዎች፣ መምህራን እና አጠቃላይ የትምህርቱ ማኅበረሰብ ወደ መማር ማስተማር ተግባሩ በድል መመለሱንም ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

በልማት ዘመቻ ማኅበራዊ አገልግሎት ስሰጡ የነበሩ የከተማዋ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ መምህራንና አጠቃላይ የትምህርቱ ማኅበረሰብ አካላት የዘማች አርሶአደርና ሚሊሻዎችን ቤተሰቦች የደረሰ የመኸር ሰብል በመሰብሰብ፣ ደም በመለገስ፣ በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ሥራዎች ከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት የታየበት ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡