ዘመን ባንክ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ

ሐምሌ 30/2014 (ዋልታ) ዘመን ባንክ አ.ማ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ጋር በመተባበር የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አካሄደ።

ዘመን ባንክ አ.ማ እና የኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ በዛሬው ቀን በእንጦጦ ፓርክ 500 ችግኞችን የተከሉ ሲሆን የተተከለው ዘጠኝ አይነት የሀገር በቀል ችግኞች መሆናቸውን የዘመን ባንክ ደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አስራት ታደሰ ተናግረዋል።

በአስቴር ጌታሁን