ኅዳር 1/2015 (ዋልታ) የስራ አጥነት ምጣኔን እየቀነሱ ዜጎች አምራችና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ትልቁ ተግባር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ የስራ ስምሪት ምክር ቤት የ2015 ዓ.ም እቅድና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መረጃ አዲስ አበባ በተያዘው ዓመት ለዜጎች የስራ እድል የመፍጠር ጉዳይ ወሳኝ ተግባር መሆኑን በመለየት በሁሉም መስክና ሴክተር የሚሰሩ ስራዎች ለዜጎች የስራ እድልን የሚፈጥሩ፣ አምራችነትንና የስራ ባህልን የሚቀይሩ፣ የክህሎትና የእውቀት ሽግግርን የሚያረጋግጡ መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ እድገትና ለውጥ ውስጥ የስራ አጥነት ምጣኔን እየቀነሱ ዜጎች አምራችና በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ትልቁ ተግባር መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
ይህም ተግባር የመንግስት ኃላፊነት ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ሃሀገር ወዳድ ባለሃብትና ድርጅቶች ተቋማት ድርሻ በመሆኑ በየደረጃው ለዜጎቻችን በፍትሃዊነትና ግልፅነት የስራ እድሎችን እየፈጠርን፣ የስራ ባህልን እየቀየርንና አምራችነትን እያበረታታን የሀገራችንን ብልፅግና ጉዞ እውን እንድናደርግ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ሲሉም አክለዋል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW