የሀረሪ ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በክልሉ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በክልሉ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

አመራሮቹ “አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ከሚገኘው ሥልጠና ጎን ለጎን ነው በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን የጎበኙት።

የተለያዩ ተቋማት የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን የዱቄትና የኦክስጅን ፋብሪካ፣ የቂሌ ኤረር ውሃ ማምረቻ ጣቢያና የአረንጓዴ አሻራ ዝግጅት ያለበት ደረጃን ተዘዋውሮ ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)