የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ለአመራሮቹ 2ኛውን ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ

ግንቦት 18/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሁለተኛውን ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

“አዲስ ፖለቲካዊ እይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ” በሚል መሪ ቃል የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ በተገኙበት ነው የተጀመረው።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ የፓርቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሥልጠናውን እንዲወስዱ በማድረግ የፓርቲውን የመሪነት ሚና፣ የመፈጸምና የማስፈፀም አቅም በማሳደግ የሕዝቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥን አላማ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ስልጠናው የተያዘለትን ዓላማና ግብ እዲያሳካ ሰልጣኞች የሚጠበቅባቸውን ዲስፕሊን እንዲያሟሉም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ስልጠናው በላቀ ተነሳሽነት ለማገልገል የተሻለ አቅም እንደሚፈጥር የገለጹት ኃላፊው በቀጣይም እስከታችኛው አባላት ድረስ ተጠናከሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት በሚኖረው ቆይታ “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ ” እና ሌሎች የሥልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW