የሀረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

ነሃሴ 21/2013 (ዋልታ) – የሀረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

በዚህም ሀገርን ለማዳን ተጋድሎ እያደረገ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልል የጸጥታ አካላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርጉ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ከሀረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡