ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – ወደ ስራ ከገባ 5አመታትን ያስቆጠረው የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ለ35ሺህ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩንም አስታውቋል፡፡
በተገባደደው በጀት አመት የሀዋሳ ኢንድርስትሪያል ፓርክ 114ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማስገባቱንም ተገልጿል፡፡
ግንባታውን በ9 ወር ጊዜ አጠናቆ በ3ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት መግባቱን ያስታወቁት የፓርኩ ስራ አስኪያጅ ፍፁም ከተማ ፓርኩ በዚህም እስካሁን ለ35ሺህ ሰዎች ቀጥተኛ የስራ እድል መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡
በፓርኩ 52 ፋብሪካዎች ሲኖሩ እስካሁንም በጨርቃጨርቅ እና ዘርፉ ላይ የተሰማሩ 23 ፋብሪካዎች ስራ መጀመራቸውን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
በይበልጥም ከፋብሪካው የሚወጣው ፈሳሽ ለአካባቢ ብክለትን እንዳያስከትል በቀን 11ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽን ወደ ንፁህ መጠጥ ውሀ በመቀየር እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከሚቋቋሙበት አላማ መካከል የእውቀት ሽግግር ተጠቃሽ ነው ከዚህ ረገድም በፓርኩ የሚሰሩ ሰራተኞችን የሙያ ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ ነውም ተብሏል፡፡
ፓርኩም ሀገሪቱ ውስጥ ካሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የመጀመሪያው የሆነ በ40ኪሜ ራዲየስ የሚደመጥ የራዲዮ ጣቢያ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡
(በሄብሮን ዋልታው)