የሀገሪቱን ዕምቅ ዐቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) – የሀገሪቱን ዕምቅ ዐቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር  የ2013 የበጀት ዓመት የክንውን ግምገማ ማጠናቀቃቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ባለፈው ዓመት በርካታ ዐበይት የስኬት ምዕራፎችን የተከናወኑ መሆናቸውን  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም አረንጓዴ ዐሻራ ማሳረፋቸውንም አስታውቀዋል፡፡