ሀገሪቱ በከፍተኛ የእድገት መንገድ እንድትጓዝ እና አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የሚያስችላት የ10 ዓመት እቅድ በካቢኔው መፅደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
የ10 ዓመት አቅድ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና መብራት ያደርጋታል ተብሏል።
እቅዱ 10 ማዕዘኖች ያሉት ሲሆን የሰላም ግንባታ እና የተቋማት ሽግግርን የተመለከቱት ልዩ ትኩረቶችን ማካተቱም ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኅትመት እና የብሮድካስት መገናኛ ብዙኃን መተዳደሪያ ሆኖ የሚያገለግለውን እና ለማኅበራዊ ሚዲያ የሕግማሕቀፍ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረውን፣ ረቂቅ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት አዋጅ ጸድቋል።
የዘርፉን ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች የሚተነትነው አዋጅ፣ የመረጃ እና የፕሬስ ነጻነት ተግባራዊነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚደግፍ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።