የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስቀጠል ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ግንቦት 1/2016 (አዲስ ዋልታ) የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርትን በመጠቀም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ማስቀጠል አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በግብዓት፣ በኢነርጂ፣ በገበያ እና በሰው ሀይል ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በተሻለ ወደ ውጤት ለመለወጥ መትጋት ይኖርባቸዋል ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።