የሁለቱ ተቋማት መግባቢያ ሰነድ

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር የፀጥታና የቁጥጥር ስራዎችን በጋራ ለመስራት የሚስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ በዛሬው ዕለት መፈራረሙን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለፁ፡፡

በ2014 ዓ.ም በማዕድን ዘርፍ ሕግና ስርዓትን ለማስከበርና ሕገወጥ እንቅስቃሴዎችን ስርዓት ለማስያዝ በትኩረት እንደሚሰራም ነው ኢንጅነር ታከለ ያስታወቁት፡፡

ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ተግባር እንደሚገባም ይሆናል ጠቅሰዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት በድንበር አካባቢዎች ሕገወጥ የወርቅ ዝውውርን ለመከላከል ጠንካራ ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ወርቅ ወይም ሌሎች ማዕድናት በሚወጡባቸው አካባቢዎች ባሉ አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ፍተሻ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡

የፀጥታ ስራዎች በተደራጀና ወጥ በሆነ መልኩ መከናወን እንዲችሉ “የማዕድን ፖሊስ ዲፓርትመንት” እንደሚደራጅም ኢንጅነር ታከለ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡