ታኅሣሥ 22/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በደቡብ ወሎ ዞን በአሸባሪው ትሕነግ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ምግብ ነክ የሆኑ ቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች በሽብር ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማትም ጎብኝተዋል።
የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ አሸባሪው ትሕነግ ባደረሰው ጥፋት በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጎድተዋል ብለዋል።
“ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች መልሶ የማቋቋም ሥራ የሁላችንም የኢትዮጵያዊያን ተግባር ነው” ያሉት ጠቅላይ ጸሐፊው፤ “ለዚህም ጉባኤው ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍል የሚውል 300 ኩንታል ዱቄት እና 600 ካርቶን ማኮሮኒ ድጋፍ አድርጓል” ብለዋል።
በቀጣይ ሁሉም የእምነት ተቋማት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ውስጥ የየራሳቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል። መረጃው የኢዜአ ነው።