የህወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልየን ብር የማበረታቻ ሽልማት መዘጋጀቱን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ፡፡
በመከላከያ ሰራዊት የህብረት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ የጁንታውን ቡድን አጋልጦ ለሚሰጥ ማንኛውም ዜጋ የማበረታቻ ሽልማት መዘጋጀቱን ገልጸው፣ ለጠቆመ አካል በልዩ ሁኔታ ከተቋሙ 10 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት እንደተመደበ ተናግረዋል።
የጁንታው ቡድንን ለመያዝ በሚደረገው ዘመቻ የትግራይ ህዝብን ጨምሮ ሁሉም ዜጋ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መቆም እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።
የጁንታውን ቡድን ለማጋለጥ የፈለገ የህብረተሰብ ክፍል ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ለፌዴራል ፓሊስ እና ለደህንነት አካላቶች መረጃዎችን መስጠት እንደሚችልም አመልክተዋል።
(በሱራፌል መንግስቴ)