የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ እና የሞጆ ከተማ ከንቲባ መሰረት አሰፋ ድምፅ ሰጡ

                                የሞጆ ከተማ ከንቲባ መሰረት አሰፋ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ እና የሞጆ ከተማ ከንቲባ መሰረት አሰፋ በሉሜ ሞጆ 2ለ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፅ ሰጥተዋል።

በምርጫ ጣቢያው 1 ሺህ 8 ሰዎች ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ ሲሆን፣ እስካሁን 800 ያህሉ ድምፅ ሰጥተዋል።

ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተመልክችያለሁ ያሉት ወ/ሮ መሰረት፣ ውጤት ከተገለፀም በኃላ “ኢትዮጵያ ትቀጥል እንጂ ማን በስልጣን ላይ ይቀጥል” መሆን የለበትም ብለዋል።

በመሆኑም ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ሁሉም ሰላሙን በመጠበቅ እና ውጤቱን በፀጋ በመቀበል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በሉሜ ሞጆ ምርጫ ክልል ሀላፊ ድሪባ ተሰማ በከተማዋ እና በገጠር ወረዳዎች አንድ ምርጫ ክልል፣ 165 ምርጫ ጣቢያ እና 825 ምርጫ አስፈፃሚዎች እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

83 ሺህ 800 መራጮች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 80 በመቶ ያህሉ ድምፅ መስጠታቸውንም ጠቁመዋል።

ብልፅግና፣ አብን እና ኢዜማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲሆኑ፣ ብልፅግና 4፣ ኢዜማ 3 እና አብን 3 እጩዎች ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት አቅርበዋል ነው የተባለው።

(በትዕግስት ዘላለም)