ሐምሌ 13/2013 (ዋልታ) – ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ2ኛ ዙር ሙሌቱን በስኬተት መጠናቀቁን ተክትሎ በዳያስፖራው የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ገልጸዋል፡፡
ዳያስፖራው ማህበረሰብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠናቀቂያ በኦንላይን ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ በተለያየ መልኩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አምባሳደር ፍፁም በማህበራዊ ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።
በዚህም ፡-
– ከዳላስ ቴክሳስ የደብረ-መንክርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን $ 7,000(ሰባት ሺህ) ዶላር
– “1 ጡብ ለትውልድ” በሚል 11 ለጋሾች በድምሩ $6,200 (ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ዶላር) በፓስተር ወርቁ ለገሰ አሰባሳቢነት
– የ’ZTruck’ ድርጅት ባለቤት $2,000( ሁለት ሺህ ዶላር)
– ዘውድነሽ አድማሱ $1,000 (አንድ ሺህ ዶላር)
– ሀሰን በሽር $1,000(አንድ ሺህ ዶላር)
በድምሩ $17,200 (አስራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ዶላር) በቼክ ለኢምባሲው ማስረከባቸውን አስታውቀዋል።