የልደታ ክፍለ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 19/2013(ዋልታ) – የልደታ ክፍለ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የምግብ እና የቁም እንስሳት ድጋፍ አድርጓል።

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ሽታዬ መሐመድ ድጋፉ ለሁለተኛ ጊዜ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ሁለት ሚሊየን ብር ወጪ ከተደረገባቸው የምግብ እና እንስሳት ድጋፍ በተጨማሪ 10 ሚሊየን ብር ክፍለ ከተማው ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

ድጋፉ ከክፍለ ከተማው ሁሉም ወረዳዎች ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎች እና ከአመራሩ የተሰበሰበ እንደሆነ ተገልጿል።

የተሰባሰቡ የድጋፍ አይነቶች ዱቄት፣ ማካሮኒ፣ ፓስታ፣ የንፅህና መስጫ ቁሳቁሶች እና 150 በጎች ናቸው።

የወረዳዎች ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች  ሽብርተኛውን ኃይል ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት የኅብረተሰቡ ተሳትፎ እና ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በቀጣይም የሽብር ኃይሉ እስኪደመሰስ ድጋፎች እንደሚቀጠል እና የልደታ ክፍለ ከተማም እስከ 50 ሚሊየን የሚደርስ ድጋፍ ለማድረግ ይሠራል ተብሏል።

(በሳራ ስዩም)