የልደታ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከ38 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

ኅዳር 11/2014 (ዋልታ) የልደታ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያሰባሰበውን ከ38 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አስረከበ።
ክፍለ ከተማው የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዌጂ ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ የክፍለ ከተማው አመራሮች በተገኙበት ሰራዊትን በግንባር ለማገዝ ዘማቾችን ሸኝቷል፡፡
የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በመጠበቅ፣ በመዝመትና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ለሰራዊቱ ደጀንነቱን በተግባር በማሳየት ላይ ይገኛል ያሉት የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሰራዊቱም ይህ የሕዝብ ደጀንነት ስንቅ ሆኖት በድል እየገሰገሰ ነው ማለታቸውን የአዲስ አበባ አስተዳደር ፕሬስ ሰክሪታሪያት መረጃ ያሳያል፡፡